ቅዱስ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ቱውፊቱን ኦርቶዶክሳዊ ሕጉን ያስጠብቅ Restore Holy Syno

  • Author:
    n/a
  • Send To:
    Ethiopian Orthodox Tewahedo Church,
  • Sponsored By:
    All concerned
  • More Info at:
ባለፉት ጥቂት ቀናት የቅዱስ ሲኖዶስን ታሪካዊ ስብሰባ ድራማ ስንከታተል ቆይተናል። መረጃዎቹም ሆነ የሰማናቸው የብጹዓን አባቶች አካሄድ ለሰሚውም እንግዳ ፣ እንደ ቤተከርስቲያን ልጆች ደግሞ አንገታችንን ያስድፋን ለጊዜውም ቢሆን በአባቶቻችን ተስፋ እንድንቆርጥ ያደረገን ነበር። አግዚአብሔር እረሰቶን ይሆንን? ብለን የጠየቅን ጠቂቶች አይደለንም። ለሁሉም ግን ልጅ አባቱን መጠየቅ ሥርዓትም ግዴታም ስለሆነ እኛም አባቶቻችን ጋር ደውለን የምንስማው እውነት ነዉ ወይ ብለን ጠይቀን? ከብጹን አበው የሰማነው ግን በሀሳብም በዓላማም አንድ መሆኑና ለቤተክርስቲያን ከመቸውም በላይ በሕብረት እንደቆሙ ተረድተናል። ያነጋገርናችው ፭ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ቀውስጦስ ፣ አቡነ መልከጼዴቅ ፣ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ አቡነ ዕንባቆም ናቸው። ሙሉ ቃለ መጠይቁን እና አቡነ ጢሞቴዎስ ለቪኦኤ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ለንጽጽር አስቀምጠነዋል ። ከዚህ በታች ይመልከቱ